liturgical -ceremony
ሥርአተ-ቅዳሴ
(liturgical -ceremony )
እንዲሁም
ሥርአተ-ቅዳሴ በአሀት ቤተክርስቲያን ዘንድ
ቅጽ 1
በዲያቆን የኋላሸት ይኸነው የተዘጋጀ
ባህርዳር -ኢትዮጵያ ፳፻፲፭
telegram @yehwi email፦[email protected]
ሊተርጂ(liturgy)
• ሊተርጂ(liturgy )ማለት በግርድፍ ትርጉሙ በህዝብ ሚደረግ ስራ(አገልግሎት )ማለት ነው።
• ስርወ ቋንቋው ከግሪክ የመጣ ነው።
• Etymology: Greek leitorgia translates Hebrew ‘Abodah’ in the LXX. Leitos comes from archaic Greek
Leos=people, and erqo=to do, to work.
• በግሪኩ leitos ማለት ህዝብ)ሲሆን erqo ማለት ደግሞ መስራት ወይንም መከወን ማለት ነው።
• በዕብራይስጥ abodah በመባል ይታወቃል ።ቅዳሴ አንድም የቅድስት ቤተክርስቲያንን ቀኖናና ዶግማ (ሥርአተ
ትምህርትን) ዜማዊ በሆነ መልኩ የምናገኝበት መንገድ ነው።
• In the New Testament Leitourgia means temple service (Zacharia, Lk. 1:23, Heb. 9:21), the giving of aid
to Christians in Jerusalem Some definitions of the term liturgy
• ቅዳሴ በሀዲስ ኪዳን የመቅደስ አገልግሎት በመባል ተጠቅሷል።(ሉቃ 1:23፣ዕብ 9:21)
• ቅዳሴ በታወቀ በተረዳ እንዲሁም በጎላ ነገር በህዝብ የሚከወንና ለእግዚአብሔር የሚቀርብ
አገልግሎት ነው።
• ማንኛውም አይነት አገልግሎት ሊተርጂያ liturgical )በመባል አይጠራም
• አንድ አገልግሎት ሊተርጊያ ለመባል የግድ በምዕመናን(ክርስቲያኖች ኅብረት) መፈጸም ወይም የግድ
የምዕመናን አንድነት መኖር ይገባዋል ።
።እንዲሁም ከቅዳሴ በላይ የሆነ አገልግሎት የለም።
• የቅዳሴንአገልግሎት ስናነሳ ዋነኛው የማይረሳው ነገር የጌታችን ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ ነው።
• የቅዳሴ ዋናው አላማ ኀብስቱንና ወይኑን እውነተኛ የጌታችን ስጋና ደም(ንጹህ መስዋዕት )እንዲሆን
ነው።ለዋጩም እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ነው።
ቅዳሴና ምስጢረ ቁርባን
• ቅዱስ ቁርባን የተቀደሰ፣ንጹሕ የሆነ ቅዱስ መስዋዕት
(sacriment ) ነው ።ቅዳሴው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ
መንፈስቅዱስ በቅድስት ቤተክርስቲያን ይመላል።
• በዚህ ስርአት በትልቁ የሚፈጸመው ምስጢር ይህ
ነው።
• ይህ ምስጢር ሰዎች በሚታየው ኀብስትና ወይን
የማይታየውን ቅዱስ ስጋና ክቡር ደሙን
ያገኙበታል።
• ይህንንም ተቀብለው የዘለአለምን ህይወት
ይወርሱበታል።
የቀጠለ
• በቅዳሴ አገልግሎት ውስጥ በአሀት ቤተክርስቲያን (sister
church )
• ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ የመስዋዕት አቀራረብ አለ
በኢትዮጵያ
• ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንም እጅግ መጽሐፍቅዱሳዊ
• የሆነ ስርአተ ቁርባን አላት። ቅዳሴ የቅድስት ቤተክርስቲያንን
• ዶግማ በተለየ መልኩ ከሌሎች አገልጎሎቶች በበለጠ ሁኔታ
• የምናውቅበት ነው።
• ቅዳሴ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
• በመደበኛነት በ5 አገልጋዮች ይከወናል። ይህም የ5ቱ አዕማደ
ምስጢር ምሳሌ ነው።
ካህናት በቅዳሴ ውስጥ
• እንደሚታወቀው አምስት አገልጋዮች በቅዳሴ ይሳተፋሉ
ከነዛም መካከል ቅዱስ ስጋውን የሚያቀብለን ዋናው ካህን
ሰራዒ-ካህን ሲባል ቀጥሎ ያለው የሚራዳው ካህን ደግሞ
ንፍቅ-ካህን በመባል የሲባይጠራል።
• ሰራዒው ካህን በቅዳሴው አገልግሎት የሰመረ ሚና አለው።
• በቅዳሴው ውስጥ አሐዱ አብ ቅዱስ ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ
፣አሐዱ ውእቱ መንፈስቅዱስ የሚለው፣ስጋዉና ደሙን
የሚፈትተው እርሱ ሰራዒው-ካህን ነው።
• እንዲሁም ቅዱስ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ
ወንጌል የሚያነበው ይኸው ሰራዒው ካህን ነው።
መልመጃ ፩
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በትክክል
መልሱ።
• የቅዳሴ ዋነኛው አላማ ምንድነው?
• በቅዳሴ ውስጥ ምን ያህል ካህናት ይሳተፋሉ?
• አንድ አገልግሎት (አምልኮ)ሊተርጂያ እንዲባል ምን
ሟሟላት አለበትት?
• በቅዳሴ ውስጥ ዋናው ካህን ማን ተብሎ ይጠራል?
በቅዳሴ የዲያቆናት ድርሻ
• ዲያቆናት በእግዚአብሔር ፈቃድ በኤጲስ ቆጶሳት
የሚሾሙና አገልግሎታቸውን ከነቀፋ ብሎም ከነውር የጸዳ
ማድረግ ይኖርባቸዋል።
• በቅዳሴ ውስጥ 3ት ዲያቆናት በመደበኛነት ይሳተፋሉ
እነሱም ዋናው ዲያቆን ማለትም ክቡር የሆነውን
የኢየሱስን ደም የሚያቀብለን ገባሬ ሰናይ
ሲባል፣ሁለተኛው ደግሞ ንፍቀ-ዲያቆን ይባላል።ሶስተኛው
ደግሞ ቀሚስ(ፍሬ ሰሞን)ተብሎ ይጠራል ።
• የዲያቆናት ድርሻ በዋነኛነት ለአገልግሎት መፋጠን
ይሆናል።
የቀጠለ
• ዲያቆናት የቅዱስ እስጢፋኖስን ፈለግ በመከተል
ያለነቀፋ፣ያለነውር፣ ቅድስት ቤተክርስቲያንን
ማማገልገልይኖርበታል።
• ዲየያቆናት ንጹህ ፣ለአንድ ሚስት ባል የሆነ፣ረብ የማይወድ
• ፣የማይሰክር ፣በሁለት ምላስ የማይናገር፣መሆን
ይጠበቅባቸዋል ።
• ዋነኛው የዲያቆናት አላማ መሆን የሚገባው ምዕመናንን
ወደ
• ምስጢራት ማቅረብ ነው።
• ዲያቆናት መንበረ-ታቦቱን መንካት አይችሉም።
• በቅዳሴ ጊዜ ጽንሐውን(የዕጣን መስዋዕት
የሚቀርብበትን )ንዋየ ቅዱስ ን ከወገቡ ነው የሚይዙት
የምዕመናን ድርሻ በቅዳሴ
• እንደሚታወቀው ቅዳሴ የምዕመናን ፣የዲያቆናት እና
የካህናት የአገልግሎት ህብረት ውጤት ነው።ለዚህም ነው
ቅዳሴ ሊተርጊያ ተብሎ መጠራት የሚችለው።
• ምዕመናን በቅዳሴ የራሳቸው የአምልኮ፣ተሰጥኦ
የመመለስ፣የመስገድ፣ስጋወደሙን የመቀበሌ ትልቅ ድርሻ
ይኖራቸዋል ።
• በዋነኛነት ቅዳሴ የሚቀደሰው ለምዕመናን ነው።
• እንዲሁም ለቅዳሴ አስፈላጊ የሆኑትን ነዋየ ቅዱሳትን ብሎም
መገበርያን ሟሟላትን ያካትታል
• እንዲሁም በቅዳሴ ሰአት በአንቃእዶ ኅሊና መቆምና
ማስቀደስ እጅግ አስፈላጊ ነው።